EDP
  • An Image Slideshow
  • An Image Slideshow
  • An Image Slideshow
  • An Image Slideshow
  • An Image Slideshow
  • An Image Slideshow
  • An Image Slideshow
  • An Image Slideshow
  • An Image Slideshow
  • An Image Slideshow
  • An Image Slideshow
  • An Image Slideshow
  • An Image Slideshow
  • An Image Slideshow
  • An Image Slideshow
  • An Image Slideshow
  • An Image Slideshow

Subscribe to our Newsletter







በደቡብ ክልል የደቡብ ምዕራብ ንዑስ ቀጠና ጠቅላላ ጉባኤ E-mail
Friday, 04 November 2011 16:32

edp_wolaita

የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(ኢዴፓ)  ባለፈው ዓመት   ባደረገው 5ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በፓርቲው መተዳደርያ ደንብ መሰረት ለሁለተኛ ጊዜ ከፍተኛ አመራሩን በአዲስ  መተካቱ ይታወሳል፡፡

በዚሁ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ  በቀረበው የመወያያ ሰነድ መነሻነት የትግል ጉዞውን ገምግሞ በድርጅታዊ አወቃቀር ላይ የታዩ ክፍተቶችን የማጠናከር ስራ አዲስ በተመረጠው አመራር እንዲሰራ መወሰኑ ያታወሳል፡፡ በውሳኔው መሰረት አዲስ የተመረጠው አመራር ኃላፊነቱን ከተረከበበት ጊዜ ጀምሮ በየክልሉ የሚገኙ ዞኖችንና የቀጠና አደራጃጃቶችን ሲያጠና ቆይቷል፡፡

በጥናቱ መነሻነትም በደቡብ ክልል በሐዋሳ ከተማ ላይ  በሐምሌ ወር ባደረገው ስብሰባ በደቡብ ክልል የደቡብ ምዕራብና  የደቡብ ምስራቅ ቀጠናዎችን በማደራጅት ንዑስ ድርጅታዊ ጉባዔ እንዲደረግ ቅድመ ሁኔታዎችን ባመቻቸው መሰረት  የመጀመርያውን ንዑስ ደርጅታዊ ጉባኤውን ቅዳሜ ጥቅምት 18 ቀን 2004 ዓ.ም የፓርቲው ፕሬዚዳንት አቶ ሙሼ ሰሙና የድርጅት ጉዳይ ኃላፊው አቶ ነጻነት ደመላሽ በተገኙበት በወላይታ ሶዶ ከተማ አካሂዷል፡፡

በንዑስ ድርጅታዊ  ጉባኤው ላይ  ከወላይታ ዞን 13 ወረዳዎች፣ ከዳውሮ ዞን 4 ወረዳዎች፣ ከኮንታ ልዩ ወረዳ ሁለት የምርጫ ክልሎች እንዲሁም ከጋሞጎፋ ዞን በከፊልና  ወደፊት በቀጠና ደረጃ በሚደረጉ ንዑስ ጉባኤዎች ላይ የሚሳተፉ አባላት የልምድ ልውውጥ እንዲያደረጉ ለማገዝ በደቡብ ክልል ከደቡብ ምስራቅ ቀጠና  ሲዳማ ዞን ከአለታወንዶ፣ ከጉጂ እና ከጌዴኦ ዞኖች የየዞኖቹ ኃላፊዎችን  ጨምሮ በጥቅሉ 30 አመራሮች  ተገኝተዋል፡፡

በዚሁ ንዑስ ጉባኤ ላይ የቀድሞ አመራሮች የሁለት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ያቀረቡና ውይይት የተካሄደበት ሲሆን፤ ኢዴፓ በከፍተኛ አመራሩ ውስጥ እያደረገ ያለውን የኃላፊነት ሽግግር  በፓርቲው የተለያዩ  መዋቅሮች ውስጥ  በተግባር እንዲለመድ ባለው እቅድ መሰረት አራት  የቀጠናውን ነባር አመራሮች በአዲስ በመተካትና ሶስት አዳዲስ አመራሮችን  መርጧል፡፡ ከተመረጡት አመራሮቹም ውስጥ ሁለት ሴቶች በምርጫ ውጤታቸው መሰረት ተካተዋል፡፡

በመካሄድ ላይ የሚገኝው ይህ ንዑስ ድርጅታዊ ጉባኤ በቀጣይ በሰሜን፤ በምስራቅና በምዕራብ ኢትዮጵያ የተለያዩ ዞኖችና ቀጠናዎች የሚቀጥል መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

 

Ethiopian Democratic Party - Election 2010 Campaign
(Photo slideshow)

edpLalibelacustom

This site is best viewed using the latest version of Firefox