|
ኢዴፓ የምርጫ ማንፌስቶውን ለሕዝብ አስተዋወቀ |
|
|
Thursday, 04 March 2010 17:56 |
|
የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ግንቦት 15 ቀን 2002 ዓ.ም በሚካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ የሚያቀርባቸውን ዋና ዋና አጀንዳዎች የያዘ የምርጫ ማንፌስቶ ለሕዝብ ይፋ አደረገ።
ፓርቲው ይህንኑ ማንፌስቶ ለሕዝብ ይፋ ያደረገው ማክሰኞ ከሰዓት በኋላ በግዮን ሆቴል በጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ መሆኑን ከስፍራው የደረሰን ዜና አመልክቷል። በዚሁ የማስተዋወቅ ስነ ስርዓት መግቢያ ላይ፣ ማንፌስቶው ከያዛቸው ዋና ዋና ነጥቦች ጥቂቶቹ በንባብ ቀርበዋል። በመቀጠልም በስፍራው ከነበሩ ጋዜጠኞች ለተነሱ ጥያቄዎች ከፓርቲው አመራር አባላት ምላሽ የተሰጠ መሆኑ ታውቋል።
በአምስት ክፍሎችና በበርካታ ንዑሳን ክፍሎች የተዘጋጀው ባለ 30 ገጽ የኢዴፓ የምርጫ ማንፌስቶ አቀራረቡ ከሌሎች ፓርቲዎች ለየት ያለና የፓርቲውን አማራጭ ሃሳቦች በግልጽ የሚያሳይ ነው ሲል የዜና ምንጩ ጨምሮ ገልጿል።
የኢዴፓ የምርጫ ማኒፌስቶ

|